ብዙ ህልመኞች በአብዛኛው ብቻቸውን መሆን ያዝወትራሉ፡፡ ነገር ግን ምክንያታቸውን ብዙ ጊዜ በግልጽ አይነግሩንም፡፡ ስለሆነም በዚህ ቪዲዮ እኒህ ህልመኞች ብቻቸውን በመሆን የሚያገኟቸውን ምስጢራዊ ጥቅሞች ለመገንዘብ እና እኛም ከዛሬ ጀምሮ የጥቅሞቹ ተቋዳሽ ለመሆን ቪዲዮውን በጥሞና እስከመጨረሳ ተከታተሉት፡፡
ብቻችንን መሆን እንለማመድ ስለ ሁለት ምክንያቶች፡-
1. አምላክ ሰራሽ ማንነታችን በተፈጥሮው ጸጥ ያለ ቦታ እና አርምሞና ተመስጦ የበዛበትን ጊዜ ስለሚፈልግ ብቻን መሆን ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ጊዜም ሰዎች በልካቸው የቀረጹት ሁከት፣ ጫጫታ ወዳጅ ጨለምተኛው ማንነታችን ቦታውን ይለቃል፡፡
2. ትላልቅ ዓላማዎቻችን፣ ራዕይዎቻች እና ህልሞቻችን ከሃሳብ ወደ እምነት እና ስሜት በመቀየር ከእንቅልፋችን ቀስቅሰው ተግባር እንድንወስድ በማድረግ ወደ ውጤት የሚቀየሩበት ብቸኛው መንገድ ብቻን መሆን ነው፡፡
Негізгі бет Тәжірибелік нұсқаулар және стиль ብቻህን ሁን / Be Alone
Пікірлер: 4