Gospel song by Singer (Pastor) Tekeste Getnet. Lord Jesus you came in to my closed house and rescued me by giving your Peace in the midst of trouble. I praise your Holy Name.
“በተዘጋ ቤት ውስጥ ገብተሃል”
በዘማሪ/መጋቢ ተከስተ ጌትነት
እንታነጽበት ዘንድ አቅራቢ
ወ/ም ሶካ
በተዘጋ ቤት ውስጥ ገብተሃል
“ሠላም ይሁን!” ለእኔ ብለሃል
ችግሬን የረሳሁብህ
ልነሳ እስቲ ላምልክህ
በተዘጋ ቤት ውስጥ ገብተሃል
ሠላምህን ለእኔ ሰጥተሃል
ችግሬን የረሳሁብህ
ልነሳ እስቲ ላምልክህ
ኮቴህ ሳይሰማ በር ሳይኳኳ
ከቤቴ የገባህ ጌታ አንተ ነህ ለካ
የት አለ ያ እጅህ ስለእኔ የደማው
ቁስሌ የተሻረበት መገኛዬ እርሱ ነው
በተዘጋ ቤት ውስጥ ገብተሃል……..
በር ዘግተን አዝነን ተቀምጠን
እንዳይገድሉን አይሁዶችን ፈርተን
ውሎ አደረ ልብ እንደዋለለ
የምንጠብቀው ጌታ ወዴት አለ
ከመከራ የሚያግዝ ሲታጣ
ቢጨላልም ቀን እስከሚወጣ
ከተፍ ሲል ባልጠበቅነው ሰዓት
ተወገደ መጨነቅ መባባት
[የሠላም ምንጭ አንተ ሠላሜ ሆይ
ለአፍታ አትለየኝ እባክህ ከቤቴ ሁን
ጌታ መገኘትህን አትውሰድብኝ
ጥጋቤ አንተው ነህ ሌላው ሁሉ ይቅርብኝ] 2
እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
Негізгі бет Музыка በተዘጋ ቤት ውስጥ ገብተሃል Betezega Bet Wust Gebtehal ተከስተ ጌትነት Tekeste Getnet
Пікірлер: 195