“ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።”
- መዝሙር 63፥3
በሰፊው ትከሻህ ተሸከምከኝ
በብዙ ትዕግስትህ ቻልከኝ
ለምህረትህ ፈጠንክ ለቁጣህ ዘገየህ
እንድመለስ ወዳንተ ጊዜን እያበጀህ
ባይመችህም የልቤ አዳራሽ ሰገነቱ
ቢቆረቁርህም መቀመጫው ዙፋኑ
ግን አብረኸኝ አለህ ዛሬም የዘመመውን ቤቴን ልታቀና
እድፋሙን ልብሴን አጥበኸው ልታቆመኝ እንደገና
አሀሀ ብዙ ነው ምህረትህ
አሀሀ ጥልቅ ነው ፍቅርህ
አሀሀ ሰፊ ነው ትዕግስትህ
አሀሀ ይገርማል መውደድህ
ደጋግሜ ስወጋው ቁስልህን
ሳሳምምህ ሳበዛው ሀዘንህን
መዳን እንዲሆንልኝ ታገስከኝ በብዙ
የምህረት እጆችህ አጥብቀህ እጄን ያዙ
ባይመችህም የልቤ አዳራሽ ሰገነቱ
ቢቆረቁርህም መቀመጫው ዙፋኑ
ግን አብረኸኝ አለህ ዛሬም የዘመመውን ቤቴን ልታቀና
እድፋሙን ልብሴን አጥበኸው ልታቆመኝ እንደገና
አሀሀ ብዙ ነው ምህረትህ
አሀሀ ጥልቅ ነው ፍቅርህ
አሀሀ ሰፊ ነው ትዕግስትህ
አሀሀ ይገርማል መውደድህ
Негізгі бет ብዙ ነው ምህረትህ - Bezu nw mihreteh Rahel Wendwesen New Ethiopian gospel song.2023
Пікірлер: 116