ለዘላለም ነግሰህ የምትኖር ግዛትህም የማይደፈር
አገዛዝህን እወደዋለሁ በቅድስና የተሞላ ነው
ስርአትህ ከጥንት የነበረው ፍጥረትን የሚያስተዳድረው
ቅዱስ ነው እንከን የለበትም ለአንተስ መገዛት አይፀፅትም
በቅድስና |2x
በንፅህና |2x
የተሞላ ነው የአንተ አገዛዝማ
አይሻሻልም ህገመንግስትህ
የረቀቀ ነው ቀድሞም ከጥንት
ግኡዙ ሁሉ የሚገዛለት ፍጥረት
የሚፈሰው ባሰመርክለት
እርሱ ምስጉን ነው የታደለ
አምላክ የሆንከው ያመነህ
ሕግህ መብራት ነው ለመንገዱ
መውጫ መርከቡ ከሞገዱ
ስርአትህ ከጥንት የነበረው ፍጥረትን የሚያስተዳድረው
ቅዱስ ነው እንከን የለበትም ለአንተስ መገዛት አይፀፅትም
በቅድስና
በንፅህና
የተሞላ ነው የአንተ አገዛዝማ
ፍትህ አይጓደል ፍርድህ አይዛባ
ፈሶ አይቀርም የምስኪኑ እንባ
እግዚአብሄር ብሎ በአንተ የፀና
ድል የራሱ ነው የኋላ ኋላ
እርሱ ምስጉን ነው የታደለ
አምላክ የሆንከው ያመነህ
ሕግህ መብራት ነው ለመንገዱ
መውጫ መርከቡ ከሞገዱ
ስርአትህ ከጥንት የነበረው ፍጥረትን የሚያስተዳድረው
ቅዱስ ነው እንከን የለበትም ለአንተስ መገዛት አይፀፅትም
በቅድስና |ፍፁም አይፀፅትም ፍፁም አዎ|
በንፅህና |ፍፁም አይፀፅትም ፍፁም አዎ|
የተሞላ ነው የአንተ አገዛዝማ
Негізгі бет Bekidesna | በቅድስና | Soreti Moges
No video
Пікірлер: 14