✞አቡነ አረጋዊ✞
አቡነ አረጋዊ ጻድቁ መነኩሴ
በኃጢአት አንዳትሞት ሕያዊቷ ነፍሴ
ጻድቁ አማልደኝ በቅድመ ሥላሴ(፪)
ከእናት ከአባት ፍቅር - - አቡነ አረጋዊ
አምላክን መርጠሀል - - አቡነ አረጋዊ
መከራ መስቀልን በእውነት ታግሰሀል
የእግዚአብሔር ቸርነት ከሞት ሰውሮሃል
አዝ= = = = =
ምስጢረ መለኮት - - አቡነ አረጋዊ
በልብ ቢመላ - - አቡነ አረጋዊ
አረጋዊ ተባልክ ሣለህ ታናሽ ጨቅላ
ጸጋህ ትደርብን ትሁንልን ጥላ
አዝ= = = = =
ከዳሞት ተራራ - - አቡነ አረጋዊ
ከማህሌት ከተማ - - አቡነ አረጋዊ
በጽዮን ዝማሬ ነፍስህ ብትጠማ
በዘንዶ ተጉዘህ ሰማህ ያንን ዜማ
አዝ= = = = =
የህግ መምህር - - አቡነ አረጋዊ
በረከት አድለን - - አቡነ አረጋዊ
ከድካም ወደ ኃይል በእምነት አሻግረን
ወደ ጌታ ደስታ በምልጃህ አቅርበን
መዝሙር
ዘማሪት ለምለም ከበደ
"ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ"
መዝ፻፵፩፥፯
💠ደብረ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ማይጸብሪ💠
Негізгі бет "አቡነ አረጋዊ ጻድቁ መነኩሴ"ዘማሪት ለምለም ከበደ የአቡነ አረጋዊ መዝሙር Abune Aregawi tsadku menekuse mezmur zemarit lemlem
Пікірлер: 52