የሚሰግዱ ድንጋዮች ያሉበት ጅሩ ቅድስት አርሴማ ጉዞ
የጉዞ ማስታወሺያ ስለ ጅሩ ቅድስት አርሴማ
ወደ ጅሩ አርሴማ መሄድ ለምትፈልጉ ከአ/አ ከተነሳችሁ የተሻለው አማረጭ በእነዋሪ መኪና በመሳፈር ደብረ ብርሃን ሳይገባ በሱሉለታ መስመር በሙከጡር አድርጎ ሲሃ ደብር መውረድ ከደብረ-ብርሃን ከተነሳችሁ ደግሞ ለሚ በሚለው መኪና በመሳፈር ሲያደብር መውረድ ወይም ከደብረ-ብርሃን ደነባ በሚለው መኪና ተሰፍሮ በሁለተኛ መኪና ወደ ሲያደብር መሄድ ይቻላል፡፡
እኔ በሶስተኛው አማራጭ ስለነበር የተጓዝኩት አረፋፍጄ 11፡ 00 ሰዓት ላይ ሲያደብር ደረስኩ፡፡ እቃ በሚሸከሙ የአገሬው ትሁታን ልጆች አማካኝነት እቃዬን አስይዤ በነሱ መሪነት ጎዞ ወደ ታላቋደብር ቅድስት አረሴማ ዘጅሩ ተጀመረ፡፡
አንድ እናት አርሴማ ለመድረስ ለደካማ 45 ደቂቃ ወይም 1፡ 00 ሰዓት ይወስዳል ነገር ግን ለበረቱት 30 ደቂቃ በቂነው ብለውኝ ነበር፡፡ ነገር ግን የአዋሳው ወደጄ ረጋ ብለህ ከተጓዝክ
3፡00 ሰዓት ትፈጃለህ ብሎኝ ስለነበር ለጉዞ ስነሳ ሁለቱ ሃሳቦች ተጋጭተውብኝ ነበር፡፡ ነገር ግን በጉዞው ያረጋገጥኩት አዋሳው ወዳጄን አባበል እውነትነት ነበር፡፡
ክፍል አንድ
በሰዓቱ ሊዘንብ ይከጅል ስለ ነበረ እሩጫ በሚባል እርምጃ ሜዳውን ጨርሰን ሸለቆውን ለመጀመር 25 ደቂቃ ወሰደብን።
ክፍል ሁለት
ሸለቆው (ገደሉ) ልክ ከፎቅ በደረጃ መውረድ ያህል ነበር፡፡ ቁልቁለቱ ጉልበት ያብረከርካል ዝም ብሎ ወደ ታች መውረድ አሁንም መውረድ ብቻ ነበር፡፡
በተለይ መንገዱ አንድ አንድ ቦታ በሁለት እግር ብቻ መውረዱን ትጠራጠሩና የቀሩትን ሁለቱንም እግራችሁን ማለት እጃችሁን መጠቀም ግዴታ ይሆናል፡፡
ለነገሩ እኔ ገና ከመነሻው የአገሬውን ልጆች በትር ይዤ ስለ ነበር በለሶስት እግር ነበርኩ፡፡ሶስቱን ስጠራጠር ደግሞ አራተኛውን እየተጠቀምኩ ቁልቁለከቱን ገፋውት፡፡
በነገራችን ላይ የቁልቁለቱ ነገር ሲነሳ ሸንኮራ ዩሀንስን ደብረ ይሰበይ አቡነ ሀብተማሪያም ገደምን ያየ ትልቅ ቁልቁለት አይቻለው ብሎ የሚል ሰው ካለ ጅሩ አርሴማ መጥቶ ቢያይ እጁን በአፉ ይጭናል፡፡
እኛ መኪና ውስጥ 30 ደቂቃ ቢፈጅ ነው ያሉኝ የደነቧዋ እመቤት ስመለስ ሁለተኛ እንደዚህ አይነት ስህተት እንደይሰሩ ሰዓት ልገዛላቸው በጉዞው ላይ ተመኝቼ ነበር። ሸለቆው አንድ ሙሉ ሰዓት ብቻውን ፈጅቶብን ቁልቁለቱን አገባደድነው፡፡
ክፍል ሶስት
ግማሽ ቁልቁለት እና ተዳፈት መሰል ሜዳማ መንገድ ለመጨረስ በተጨማሪ 30 ደቂቃ ወስዶብን በአጠቃላይ መንገድ ላይ አንዴ ከአረፍንበት ጭምር ጥሩ ተጓዥ በሚያሰኝ አከሄድ ከሁለት ሠዓት የእግር ጉዞ በኋላ ተምረኛዋ ደብረልዕልና ቅድስት አርሴማ ደብር ወደ አንድ ሰዓት ገደማ ደረስን፡፡
ልክ አርሴማ ስትደርሱ እግር አጥበው መዝግበው የማረፍያ ስፍራ ይሰጡዋችዋል፡፡ እኔ የደረሰኝ አደራሽ ተብሎ በተለምዶ ከሚጠራው የፀሎት ቦታ በረንዳው ላይ ነበር፡፡
ይህንን ሁሉ ገዳል ወርጄ በግምት ከሁለት መቶ ሰው በቦተው ላይ ስመለከት በጎዞው ተፈጠረው ድካም ልክ እንደ ጉም በኖ ጠፋ፡፡
በተሰጠኝ ቦታ አነጣጥፌ በቀድሞቹ መጪዎች በተደረገልኝ የትህትና አቀባበል እየተደሰትኩ ጎኔን ከመሬት ጋር ወደ ሶስት ሰዓት ገደማ አገነኘውት፡፡
ከተመለከትኩት እና ከአስደነቁኝ ነገሮች መሀከል እዛ ካለው ሰው ከአንድ ሶስተኛው የመንፈስ ችግር አለበት፡፡
አብዛኛው ደግሞ ዛር፤ ውቃቢ ፤ቃልቻ የሚባለው የሰይጣን አይነት ነው፡፡ በእርግጥ ሌሎችም ህመምተኞች ቢኖሩም እነዚህ ግን ቦታው ይልቃሉ፡፡
ከእነሱ መሀል ጥቂት የሚያስቸግሩም በለሰንሰላቶች ቢኖሩም አብዛኞቹ ግን ሰው ሳያስቸግሩ ወደ ገደልም እንግባ ሳይሉ የሚኖሩ መሆናቸውን ስታዩ የእግዚአብሔር ጠብቆት ምንያህል ከሰይጠን ክፋት በላይ መሆኑን ትረደላችሁ፡፡
እንደሁም የሚያመውን ሰው ምትለየዩት በፀሎት ሰዓት የሚሆነው ካያችሁ በሃላ ነው፡፡ እንደው ደህና መስላቹ ሲያጫውታችሁ ውልና በመሃከል ከት ብሎ ስቆ እኔ እኮ ሰይጣኑ ነኝ አሳ ወይም እሱ አይደለም ብሎ ሊስቅባችሁ ስለሚችል ጤነኛውን ከባለመንፈሱ ለመለየት ዋል አደር ማለት ይጠይቃል።
እዚህ ቦታ ከሚያስገርመው አንዱ ደግሞ ይህን ያህል ሰው እንዴት አንደመጣ ስታጣሩ ተልከው እንደመጡ ትሰማላችሁ፡፡ ከዬት ብትሉ ከፃድቀኔ ማርያም፤ ሽንቁሩ ሚከኤል፤ከመሳሰሉት የሚል ይሆናል፡፡
በነገራችን ላይ ከዚህ ተልከው ወደ ሌላ ቦታ የሚሄዱም አሉ፡፡ ለምሳሌ ወደ ታላቋ የወሎ ሲርንቃ አርሴማ ገዳም የተላኩና የወጡ ሰዎች በብዛት አይቻለው፡፡
እንዴት ነው መልዕክቱን የሚያገኙት ብትሉ?? በሁለት አይነት
መልኩ የሚለው መልስ ይሆናል ፡፡ ይህም ማለት አንዱ በራዕይ ሁለተኛው ደግሞ መንፈሱ ሲለፈልፍ መውጫውን ቦታ ስለሚጠቁም ነው። በነገራችን ላይ ይህ ነገር የሆስፒታሉን referral system አስታውሶኛል፡፡
አንዳንዶች እንደውም ሰማእቷ ከረዳችኝ መልሱን አገኛለሁ ካለሆነም referral ይጻፍልኛል ይላችኋል ፡፡አይገርምም ????
ሰማእቷ ቅድስት አርሴማ የምትታወቀው ዘንባባ በመያዟ ሲሆን ( በነገራችላይ ጽዋ የያዘችውን ስዕል በአብዛኛው በኢትዮጵያ የአርሴማ ሚባለው የቅድስት ባርባራ ስዕል መሆኑን እዚ ላይ ያጠይቅዋል ) ታዲያ በድብሩ ዙሪያ ያሉ ድንጋዮች ተፈንቅለው ሲከፈሉ የዘንባባ ምስል መገኘቱ የቦታውን ታምራተኛነትን ያረጋግጣል።
እንደሁም አንዳንዱ በቅጠል ቅርጽ ዘንባባውን እያስቀረጹ ፊቱን መስቀል በማድረግ በስተው ማንጠልጠል የተለመደ ሲሆን እኔም ለበረከት አንድ ሁለት ደርሶኛል በደበሯ ሁሉም ሰው የሚጠቀምበት አንድ ብዙ ሰው የሚያስተናግድ ሽንት ቤት ነበር፡፡
አሰራሩ በተራራ ጫፍ ላይ ስለነበር ከስራ ጥራቱ ጉድለትም በላይ ንፋስ የሚወዘውዘው በመሆኑ የሚያሰጋ ሽንት ቤት ነበር፡፡በቀን 1/13/2003
በማታ የአንድ ሰአት ጸሎት ላይ ፤ሁሉም ምህላ ገብቶ በነበረ ጊዜ የተወሰኑ ሰዎች የጸበል ብዛትም ይሁን የሆድ እክል ሲያስቸግራቸው ሽንት ቤት ገብተው ጉዳያቸውን ፈጽመው እንደወጡ ሽንት ቤቱ ፈረሰ፡፡ ወይም በቀላል ቋንቋ ሰጠመ።
ነገር ግን አንድም ሰው ላይ አደጋ አለማጋጠሙ ትልቅ ድንቅ ተአምር ነበር ፡፡ እንዴት ብትሉ????
ከመጨረሻዎቹ ወንድ ተጠቃሚዎች መሀከል አንዱ ሽንት ቤቱ ከመሰጠሙ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት እዛ ሆኖ ዛሬ ይቺን ሽንት ቤት ምን ያርገበግባታል?? ሲል እንደነበር የሰሙት ሰዎች ነግረውኛል።
በተለይ ሽንት ቤቱ ሲፈርስ የተፈጠረው ድምጽ የጸሎት አዳራሽ በመሰማቱ ጸሎቱን ከደጅ ከሚሳተፉት መሃከል ሰው አብሮ ሰጥሞ ይሆናል ያሉ የተወሰኑ ሰዎች እየተራራጡ ሽንት ቤቱ ቢደርሱ እዛው የነበረችው የመጨረሻዋ ተጠቃሚ በኩራት ( በኮንፊደንስ ) አትደንግጡ እኔነኝ የመጨረሻዋ
ተጠቃሚ ብላ መጪውን ሰው አታረጋጋውም!!!!!!!! ድንቅ የእግዚአብሔር ተዓምር አትሉም???
ወይ አርሴማ በደጇ መጥቶ የሚማጸነውን ትፈውሳለች እንጂ ሽንት ቤት እንደማትጨምር አረጋግጣ ተአምሯን አሳየች!!!!!!!
ደብሯ ከጸበል አገልግሎት ውጪ በዋናነት የአርምሞ የሱባኤ ስፍራ ናት ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጁ ሁለት ዋሻዎች አሉ ፡፡
አንደኛው በጣም ሞቃት ሲሆን ሌላኛው በጣም ቀዝቃዛ ነው
በዋሻው የቆይታ ጊዜ በቀን መውሰድ የሚቻለው አንድ በውኃ የራሰ እፍኝ ሽንብራ እና አንድ ኩባያ በሶ ብቻ ይሆናል ውኃ የሚፈልግ በሶውን ትቶ በአንድ ኩባያ ውኃ መቀየር ይችላል።
በቅደስት አርሴማ የቆይታ ጊዜው ከሌሎች የሱባኤ
ስፍራዎች ይለያል። መልስ ያገኘ በማግስቱም ይወጣል ያላገኘ ወይም ቆይ የተባለ ደግሞ ይቆያል ነገር ግን የሱባኤው ትንሹ ቀን ሶስት ቀን ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል ፡፡
ሱባኤ መግባት አብዛኛው ሰው የሚያደርገው የተለመደ ጉዳይ ሲሆን ይልቁን መንፈሳዊ ልምምድ የሌላቸው ጫትና መጠጥ ትተው አሁን እንደመጡ አደራሽ ውስጥ ሲናገሩ የሰማኋቸው አፋቸው ላይ ጨርቃቸውን አስረው በዚህ ቅዱስ ስፍራ ሳያቸው
መለወጣቸው አስገርሞኝ ኦርትዶክስ ለዘላለም ትኑር ብዬ ልጮህ ከጅሎኝ ነበር ፡፡ ነገር ግን እኔም አርምሞ ላይ መሆኔ ትዝ ሲለኝ........ ተውኩት
በነገራችን ላይ የዋሻው የውስጠኛው ክፍልን አላስተዋወቅካችሁም አይደል ??? ዋሻው ከውስጡ ሲታይ የሚመስለው......... ይቅርታ......ተውት...... ለካ ዋሻው ይታያል እንጂ አይተረክም።
Негізгі бет ድንቅ ነው የሚሰግዱ ድንጋዮች ያሉበት ጅሩ ቅድስት አርሴማ
Пікірлер: 186