. ✝ ✝ ✝
✝️ የጋብቻ ዋና አላማው መጽደቅ ነው ። ✝️
" እርሾው መልካም ከሆነ ቂጣው መልካም ይሆናል ሥሩ ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፉ ቅዱስ ይሆናል ሥሩ መራራ ከሆነ ቅርንጫፉም መራራ ይሆናል" ሮሜ 11፥16
👉ምን ማለት ነው ?
✞ትዳሩ ከተቀደሰ ልጁ ቅዱስ ይሆናል ። እየሰረቃችሁ የማይሰርቅ ልጅ አትፈልጉ ።እያመነዘራችሁ ድንግል ልጅ አትፈልጉ ። ክፉዎች ሁናችሁ አንድነት የሚፈልግ ልጅ አትፈልጉ ።
✞መተዋወቅ መጠናናት እያላችሁ በኃጢአት አትውደቁ ።
✞በየሜዳው በየኢንተርኔቱ ትዳር አትፈልጉ።
✝ ✝ ✝
✝በዓለም ላይ ሦስት በሽታዎች አሉ ይላል ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ✝
👉ድንቁርና
👉ስንፍና
👉መርሳት
ሰሞኑን ለምሳሌ በኢትዮጵያ አንድ ሰው ሙቷል ። አንድ ሰው ሞተ ብሎ ሁለት መቶ ሦስት መቶ ሰው መግደል ድንቁርና አይደለም ? በአንድ ሰው ሞት የቆረቆረው ሰው ሁለት መቶ ሰው ይጨምራል ? እግዚአብሔር ከእንዲህ ያለ ድንቁርና ይሠውረን። አሜን....አምላክን ለመስቀል ያበቃ ድንቁርና ነው ። ክርስቶስን በሠላሳ ብር ለመሸጥ ያበቃ ድንቁርና ነው። እንደ ድንቁርና ያለ ክፉ በሽታ የለም በእውነቱ ።
✞የንጉስ ልጅ ስትሆን እያደርክ የሚያከሣህ ምንድን ነው ?
✞ወንጌልም ገድል ናት ።
✞የሚሞቱ ክርስቲያኖች ለቤተክርስቲያን ሰቀቀኖቿ አይደሉም ፤ ክብሮቿ ናቸው ።
✝ ✝ ✝
✝👉'የቅዱሳንን ገድል አታንቡ ፤ የክርስቶስ ክብር ይሸፈናል ፤የእግዚአብሔር ክብር ይሸፈናል' የሚሉ የአውሬው ልጆች ሞልተዋል በዓለም ላይ ....
👉የሉቃስ ወንጌል ገድለ ቅዱሳንን የሚያበስር መጽሐፍ ነው። ገድለ ቅዱሳን ለመጻፉ ዋናው ማስረጃው አንዱ የሉቃስ ወንጌል ነው።
👉"የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ይሄን ያህል ቅዱሳን አያማልዱም ይላል" ይላል ይሄ ጅሉ "የማቴዎስ ወንጌል" እያለ ፤ ወንጌሉን በማቴዎስ ስም እየጠራ "የዮሐንስ ወንጌል" እያለ ፤ ወንጌሉን በዮሐንስ ስም እየጠራ 'ማቴዎስ አያስፈልግም' ፣ 'ዮሐንስ አያስፈልግም' የሚል እንዲህ ያለ ድንቁርና ነው ።
✝ ✝ ✝
👉#subscribe በማድረግ ይከታተሉ ።
• Video
👉#share በማድረግ ለሌሎች ያዳርሱ።
👉#አገልግሎቱንም ይደግፉ።
Негізгі бет አዲስ እጅግ ድንቅ ትምህርት "ብዙዎች በልደቱ ደስ ይላቸዋል" በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገ/ኪዳን ግርማ
Пікірлер: 82