#Ethiopia;_አጋንንትን_የሚያሳድድ_ፀሎት
ጸሎቱን በሰቀቀን ሳይሆን በፍቅር እንዴት መጸለይ እንዳለባችሁ እንመለከታለን፡፡
ወዳጆቼ በጸሎት ዙርያ እጅግ ቅር የሚለኝን ነገር ልንገራችሁ፡፡ ይህም አብዛኞቻችን የመላእክት፣የቅዱሳንና የሰማእታትን ጸሎቶች ጠንክረን እንጸልያለን፡፡ ይህ መልካምና ተገቢም ነው፡፡ ግን ማንን ይዞ ጉዞ ነውና እኛን አክብረው፣በራሳቸው አምሳል የፈጠሩንን ቅድስት ሥላሴን ዘወትር በጸሎት አለማመስገንና፣በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አባቶቻችን የደረሱትን ለቅድስት ሥላሴ የሚቀርበውን ጸሎት አለማድረስ በሰማይ የሚያስወቅስ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ቃል ኪዳን ሰጪ እና አክባሪ የሆኑትን ሥላሴን ሳይሆን ቃል ኪዳን ተቀባዮችን ነው የምናመሰግነው፣መታሰብያቸውንም የምናደርገው፡፡
በጥር ዜና ሥላሴ ላይ እንዲህ የሚል ተጽፏል ‹‹የጻድቃን የሰማዕታት ስም ሲጠራ ስማችን ለምን ቀረ፡፡ የጻድቃን የሰማዕታት ዝክራቸው ሲደረግ ያለ እኛ ስም ማዳን ይችላሉን? የሎሌ ስም ሲጠራ የጌታ ስም ለምን ቀረ? ሎሌስ ከጌታ በታች ከመሆን አይውጣ፡፡ ከጌታ የሚበልጥ ባርያ የለም፡፡ ለሰማዕታትና ለጻድቃን ኪዳንን የሰጠን አይደለምን? እነሱ በእኛ ስም ተጋድለዋልና፡፡ ሰው ሆይ አስቀድመህ ስማችንን ጥራ፡፡ ከዚህ በኃላ የሰማዕታትና የጻድቃንን ስም ጥራ፡፡ እነሱ በስማችን አጋንንትን ያወጣሉ፣ጣዖታትንም ድል ይነሳሉ፣ቁጥር የሌለው ተአምራትን ያደርጋሉና፡፡ እኛ ከእነሱ ጋር ዘወትር በየጊዘው ሁሌም እንኖራለን፡፡ የጻድቃንና የሰማዕታትን ፈቃዳቸውን የምንፈጽምላቸው እኛ አይደለምን? ሰው ስማችንን እንደምን አያከብርም? አለቆቻቸውና መላእክት ሲያመሰግኑን ሰዎች ግን አያመሰግኑንም›› ይሉናል፡፡ ወዳጆቼ በአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ፊት የሚያስወቅስ የሚያስከስስ ሥራ ሳይሆን የሚያስመሰግን፣ሰማያዊ ዋጋ የሚያሰጥ ሥራ መሥራት ማለት ሥላሴን በጸሎት ማመስገን፣ስማቸውን ዘወትር መጥራት እና መታሰብያቸውን ማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ እኛም በሰይፈ ሥላሴ የምስጋና ጸሎት የሥላሴት ስም መጥራት ተቀዳሚ ተግባራችን ይሁን፡፡
Негізгі бет #Ethiopia;- አጋንንትን የሚያሳድድ ፀሎት
Пікірлер: 1,8 М.