ገና
የኃላዬን እረስቼ
ሀዘን ትካዜ ትቼ
ልሩጥ ከፊቴ ላለው
ገና ነው ገና ነው
በእኔ የተጀመረው
1 ቀኑ ከፊት ሲሮጥ መመለስ የኃሊት
ለሽንፈት ከለላ መቆምሚያ ሆነለት
እንግዲያው ልነሳ ስለላቀው ዋጋ
ትላንትን ዘንግቼ ለነገ ልዘርጋ
የምን ማፈግፈግ ነው የምን ተባ ፈራ
በእኔ የሚሰራ እያለ ብዙ ሰራ
የምን ያዝ ለቀቅ የምን ተስፋ መቁረጥ
ውድቀቴን የሚመኝ ወሽመጡ ይቆረጥ
ገና እሄዳለው
ገና እወርሳለው
ገና እሰፋለው
ገና እበዛለው
2 ውጊያው ጦርነቱ ሰልፉ ቢበረታ
ኸረ እጄን አልሰጥም በስሙ አልረታ
ከእኔ ጋር ያለው ከሁሉ ይበልጣል
አሸናፊው ጌታ ድልን ይሰጠኛል
በእናቴ ማህፀን ሳለው የመረጠኝ
ልኬንና ጥጌን ወስኖ የሰጠኝ
የነገረኝ አለ ትሆኛለሽ ብሎ
ወደ እዛ እንዳልደርስ ኸረ ማን ከልክሎ
ገና እሄዳለው
ገና እወርሳለው
ገና እሰፋለው
ገና እበዛለው
እሮጣለው እሄዳለው
ወደ አየልኝ እደርሳለው
እተጋለው እበረታለው
ምልአቴን እውርሳለው
ወገቤን ልታጠቅ ገና ገና
መቼ ጀመርኩና
እዘረጋለሁኝ እስከምድር ዳርቻ
ይናገረኝ እንጂ ቃል ይኑረኝ ብቻ
ገና እሄዳለው
ገና እወርሳለው
ገና እሰፋለው
ገና እበዛለው
Song written By
#Eyerusalem_Negiya_Jerri 19/12/2010
#GENA #ገና
Music arrangement
Mezmur dawit
Mix
Abenezer Tafesse
Harmony
Illasha fekadu
background vocals
Bethlehem Alessa
Illasha Fekadu
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። የዮሐ 3:16
ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥ ገላ 1:15-16
EYEUSALEM NEGIYA'S Offiical youtube channel subscrib / @eyerusalemnegiyaoffic...
EYRUSALEM NEGIYA'S Facebook page
/ enegiya
instagran== / contact
i=g4yqsjg3t9e5&
TELEGRAM CHANNEL== t.me/JerriNegiya
Негізгі бет GENA ገና Eyerusalem negiya(jerri) official video
Пікірлер: 93