#ነሺዳ #ሚንበር_ቲቪ #Minber_TV
🌴🌴🌴
አንነቢ ሰሉ ዓለይህ
ሰለዋቱ ‘ሏህ ዓለይህ
🌴
አንነቢ ሰሉ ዓለይህ
ሰለዋቱ ‘ሏህ ዓለይህ
ወየናሉል በረካት
ኩሉ መን ሶላ ዓለይህ
ኩሉ መን ሶላ ዓለይህ
🌴
ሰለዋት ሰላም ይውረድ
በነቢ በሙሐመድ
አብቦ እየፈካ
ያውደን በበረካ
🌴
ዘመን ተሻግሮ የስምሁ አስኳል፣
በአዛን በሶላት ልቤን ያንኳኳል።
ዘልዓለም አዲስ የእኛ ሙሽራ፣
ሱናሁ ‘ማይነጥፍ ህያው አሻራ።
🌴
የአንቱ ለመባል ምን ባጠራጥር፣
ዑመት ተብዬ ገባሁ ከቁጥር።
በውድቀት እሳት ነፍሴ ተጋግራ፣
ቀኝ ስትሉኝ ዋልኩኝ በግራ።
🌴
አዘቅዝቃ የዕድሜዬ ጀንበር፣
ሩሄ ከስታ ውስጤ ሲሸበር፣
ከቀብሬ አፋፍ እየተጠጋሁ፣
አሻራዎን ለምን ዘነጋሁ፣
🌴
ተራዬ ላይቀር ሞት መሳፈሩ፣
ከስር መሆኔ ከላይ አፈሩ።
ተቀጣ ቢለኝ ያኔ ቀስቅሶ
ምን ይረባኛል የፀፀት ለቅሶ።
🌴
የአላህ ሰላት‘ ሰላሙ
በፍጥረታት ቀለሙ
በውቡ በሙስጠፋ
በረካው እንዳይጠፋ (2X)
🌴
አንነቢ ሰሉ ዓለይህ
ሰለዋቱ ‘ሏህ ዓለይህ
ወየናሉል በረካት
ኩሉ መን ሶላ ዓለይህ
ኩሉ መን ሶላ ዓለይህ
🌴
ሰለዋት ሰላም ይውረድ፣
በነቢ በሙሐመድ።
አብቦ እየፈካ፣
ያውደን በበረካ።
🌴
ሳያዩኝ ናፍቀው ሰማሁ ማልቀሶን፣
ለነፍሴ አድሬ መች ሰማሁ እርሶን።
ተናገር ብባል ውሎህን ፃፋት፣
ሐፍረት ነው ቃሌ አንገቴን መድፋት።
🌴
በብክነት መንደር ብንደፋደፍም፣
ተዳፈነ እንጂ የሙሀባው ፍም።
የልቤ ደጃፍ ቁልፉም አይላላ፣
ባንቱማ ቦታ አይገባም ሌላ።
🌴
ስውር ህመም የኔ መከራ፣
ፈውሴን የራቅኩ ያንቱን አሻራ፣
የትም ያለሁ ያጣሁ መድረሻ፣
ወዴት ይሆን የኔስ መሸሻ።
🌴
ነቢ አልኩኝ አዚሜም ፅፌ፣
ውዳሴ ሞላሁ ቃል አንጠፍጥፌ፣
የታይታ ሆኖ እንዳይቀር ‘ካፌ፣
ላኪው ፊት መጣሁ ተውበት ታቅፌ።
🌴
የአላህ ሰላት‘ ሰላሙ
በፍጥረታት ቀለሙ
በውቡ በሙስጠፋ
በረካው እንዳይጠፋ (2X)
🌴
አንነቢ ሰሉ ዓለይህ
ሰለዋቱ ‘ሏህ ዓለይህ
ወየናሉል በረካት
ኩሉ መን ሶላ ዓለይህ
ኩሉ መን ሶላ ዓለይህ
🌴
ሰለዋት ሰላም ይውረድ፣
በነቢ በሙሐመድ።
አብቦ እየፈካ፣
ያውደን በበረካ።
🌴
እንደባከንኩ የቀረሁ ሜዳ
ያሻራዎ ወራሽ ባለ ዕዳ
የምጠጋው ያጣሁ ፋና
የዋተትኩኝ ስቼ ጎዳና
🌴
ዱንያን ብዬ ዓለሜን ያጣሁ
በኒዕማዬ ቆሜ ተቀጣሁ
ለመንገድዎ ስንዝር ብጠጋ
በተረፍኩኝ ባላጣሁ ዋጋ
🌴
ከአንቱ ጎዳና መልሱን ባላጣም፣
ፈለጎን ስቼ ተቀጣሁ በጣም።
ውሎየ ሆኗል ከራስ መጣላት፣
ዛሬ ቃል መግባት ነገ ለመክዳት።
🌴
ስሸርፈው ብከርም ያንቱን አሻራ፣
ባጎድል አማና ባመክን አደራ፣
ነገዬን ባላውቅ እያልኩኝ እንጃ፣
መድረሻዬ ግን የአንቱው እርምጃ።
🌴
አንነቢ ዛከ ረሱል፣
ዚክሩሁ ዩሕዪል ዑቁል፣
ኩሉኩም ቁሙ ነቁል፣
ሶላዋቱላህ ዓለይህ።
🌴
አላሁመ ሶሊ፣
ወሰሊም ወባሪክ ዓለይህ።
🌴🌴🌴
Copyright @MinberTV
👨👩👧👦 Join Minber Family 🔗 t.me/Minber_Me...
★★★★★
የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ሊንኮች👇🏽 ይወዳጁን 👍🏽 ያጋሩ ⤴️
📍KZitem 👉 / @minbertv1
📍Facebook👉 / minbertv
📍Telegram👉 t.me/minbertv
📍TikTok 👉 / minber_tv
📍Instagram 👉 / minbertv
📍X / Twitter 👉 / minbertv
📍Website 👉 www.minbertv.com
Негізгі бет ሕያው አሻራ || ምርኩዝ 28 || "የከውኑ ሞገስ 6" || የኅብረት ነሺዳ || New Ethiopian Neshida
Пікірлер: 206