ኑሮ
ችላ አልልም መመረጤን
አላራክስ ውድ ህይወቴን
አመፅ አይሆንም ምልክቴ
እምነቴ ህያው ነው በድርጊቴ
ክብር ስላለኝ ለመጠራቴ
ቸልታ አይነግሥም ቤቴ
በጸጋህ ከመደነቄ የተነሳ
ምኞቴን ስተው አልሳሳ
አዲስ ዘር ውስጤ ስላለ
የማይቻል ኑሮ ለእኔ ቀለለ
በማዳንህ ደስታ ስለረካሁ
የጥፋት ሩጫዬን ፈቅጄ ገታሁ
ይህ ዓለም አንተን እንዲያውቅህ
በመኖር ልዩነት ልግለፅህ
ብርሃን ልሁን በብርሃንህ
በአንተው ህይወት ላክብርህ
እየተቆረስሁ ባስቻልኸኝ ሁሉ
ያጡ የጎደሉ እንዲሞሉ
በአንተ ከመኖሬ የተነሳ
ስምህ በደግ ይነሳ
ለመፈቀሬ ካለኝ ክብር
ሥጋን ማቅበጤ ይቅር
በጸጋህ ከመደነቄ የተነሳ
ኮተቴን ስጥል አልሳሳ
ልንፃልህ ይጥራ መልኬ
ላፍቅር እንዳምላኬ
ትረስርስ ትሙላ ነፍሴ
ይሰልጥን መንፈሴ
እስክትመጣ እስካገኝህ
በአካል እስክንተያይ
በገባኝ መጠን ልኑር
ልሁን ትጉ አገልጋይ
ክብር ስላለኝ ለመጠራቴ
ቸልታ አይነግስም ቤቴ
በጸጋህ ከመደነቄ የተነሳ
ዓለምን ስተው አልሳሳ
ለመፈቀሬ ካለኝ ክብር
ሥጋን ማቅበጤ ይቅር
በጸጋህ ከመገረሜ የተነሳ
ምኞቴን ስጥል አልሳሳ
Негізгі бет Illasha Fekadu - ኑሮ / Nuro
Пікірлер: 37