Gospel song by Singer (Pastor) Endrias Hawaz.
Praise be to God.
"ክብር ይሁን ክብር"
በዘማሪ/መጋቢ እንድሪያስ ሐዋዝ
እንታነጽበት ዘንድ አቅራቢ
ወ/ም ሶካ
ኃጢአተኛውን አስበኼዋል
በደምህ አጥበህ አንጽተኼዋል
ከጻድቃን ማኅበር ቀላቅለኼዋል
ከሳሹ ጠላት ዲያብሎስ አፍሯል
ለዚህ ለሥራህ ምን ይከፈላል?
ክብር ይሁን ክብር /2
በላይ በሰማይ ዙፋኑ ላይ
በታች በምድር ለእግዚአብሔር
ክብር ይሁን ክብር /4
በጠላት ቆስሎ የደከመውን
ሸለቆ ወድቆ ያለቀሰውን
ዛሬ በደስታ ሊዘምር ወጥቷል
አንተ ድንቅ ነህ ምን ይሳንሃል?
ጌታዬ ላንተ ክብር ይገባሃል
ክብር ይሁን ክብር /2….
ደረቁን ምድር አረስርሰኼዋል
የተራቆተውን አንተ አልበሰሃል
በታሪክ ማኅደር ያልታወቀውን
አንተ አስጠግተህ አገነንክ ስሙን
ጌታዬ ክብሩ ለአንተ ይሁን
ክብር ይሁን ክብር /2….
ዙፋኑ ከጥንት የዘለዓለም
ብርቱ ተዋጊ እንዳንተ የለም
የጠላት ምክር አፍርሰኼዋል
በአንድ ላይ መጥተው ተበትነዋል
ጌታዬ ላንተ ክብር ይገባሃል
ክብር ይሁን ክብር /2….
እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
Негізгі бет ክብር ይሁን ክብር Kibir Yihun Kibir ዘማሪ መጋቢ እንድሪያስ ሐዋዝ Endrias Hawaz
Пікірлер: 5