Join this channel to get access to perks:
/ @ze-ethiopia
ዛሬ መስከረም ፲፩/፯/፳፻፳፪ ዘመነ ሔኖክ ነው ።
ይሄውም ለሦስት ቀን የሚከበረው የምስጋና ቀን :- ዛሬ ካዕላይ የምስጋና ቀን "በወጣቱ ትውልድ" እና አንደበት "በወጣቱ ስም" ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ምስጋና ነው ።
መዝሙር ፻፴፭ ፡፻፴፮
፩፤እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፤ቸር፡ነውና፥ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና።
፪፤የአማልክትን፡አምላክ፡አመስግኑ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና።
፫፤የጌታዎችን፡ጌታ፡አመስግኑ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፬፤ርሱ፡ብቻውን፡ታላቅ፡ተኣምራትን፡ያደረገ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፭፤ሰማያትን፡በብልኀት፡የሠራ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፮፤ምድርን፡በውሃ፡ላይ፡ያጸና፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፯፤ብቻውን፡ታላላቅ፡ብርሃናትን፡የሠራ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፰፤ለፀሓይ፡ቀንን፡ያስገዛው፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፱፤ለጨረቃና፡ለከዋክብትም፡ሌሊትን፡ያስገዛቸው፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም
፡ነውና፤
፲፤ከበኵራቸው፡ጋራ፡ግብጽን፡የመታ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፲፩፤እስራኤልንም፡ከመካከላቸው፡ያወጣ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፲፪፤በጸናች፡እጅ፡በተዘረጋችም፡ክንድ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፲፫፤ቀይ፡ባሕርን፡በየክፍሉ፡የከፈለ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፲፬፤እስራኤልን፡በመካከሉ፡ያሳለፈ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፲፭፤ፈርዖንንና፡ሰራዊቱን፡በቀይ፡ባሕር፡የጣለ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፲፮፤ሕዝቡን፡በምድረ፡በዳ፡የመራ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፲፯፤ታላላቅ፡ነገሥታትን፡የመታ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፲፰፤ብርቱዎችንም፡ነገሥታት፡የገደለ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፲፱፤የአሞራውያንን፡ንጉሥ፡ሴዎንን፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፳፤የባሳንን፡ንጉሥ፡ዐግን፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፳፩፤ምድራቸውን፡ርስት፡አድርጎ፡የሰጠ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፳፪፤ለባሪያው፡ለእስራኤል፡ርስት፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና።
፳፫፤እኛን፡በመዋረዳችን፡ዐስቦናልና፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፳፬፤ከጠላቶቻችንም፡እጅ፡አድኖናልና፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፤
፳፭፤ለሥጋ፡ዅሉ፡ምግብን፡የሚሰጥ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና።
፳፮፤የሰማይን፡አምላክ፡አመስግኑ፤ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና።
ይምሐረነ ወ ይሠሐለነ በርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖት ያጽንዓነ ።
ለይኩን! ለይኩን ! ለይኩን!
እንኳን አደረሰን ።
Негізгі бет ካልአይ፪ የምስጋና ቀን
Пікірлер: 9