Halwot Worship Ministry is dedicated to bringing people into the presence of God through intimate worship songs. Our goal is for all people to experience the presence and get closer to the Lord Jesus, our savior!
ሀልዎት የአምልኮ አገልግሎት ዋነኛ አላማ ሰዎች ሁሉ የእግዚብሔር መገኘት እንዲታወቃቸው ማድረግ ነው! በምንዘምራቸውም የአምልኮ ዝማሬዎች ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አዳኛቸው እንዲጠጉና እንዲቀርቡ ማገዝ ነው!
ይህ ቪዲዮ በRing View Studio ውስጥ የተቀዳ ሲሆን መዝሙሩ ደግሞ በHalwot Studio ውስጥ ተቀናብሮና ተዘጋጅቶ ወደ እናንተ ቀርቦአል!
ለበለጠ መረጃ : 0911229669 ይደውሉ!
Lyrics
ማንም የማይደፍነውን
ምንም የማይሞላውን
ባዶነቴን ሁሉ የሱስ ትሞላለህ
በመገኘትህ ታጠግበኛለህ
በህልውናህ ታጠግበኛለህ
ካንተ ጋር ካንተ ጋራ ስሆን
የፊትህ ብርሃን የፊትህ ደስታ
የነፍሴ ጥጋብ ነው የነፍሴ እርካታ
ዙሪያው ዝም ፀጥ ሲል
ውስጤ ይፈልግሃል/ልቤ ይናፍቅሃል
ለብቻዬ ሆኜ አንተን አስባለሁ
በፍቅርህ ዘይት ረሰርሳለሁ
ቋንቋ አይገልፀውም የሚሰማኝ ስሜት
ከኔ ጋር እንዳለህ ለነፍሴ ሲታወቃት
በምድራዊ ነገር አይችልም ሊለካ
ያየ ነው ሚገባው በፍቅርህ የተነካ
Негізгі бет ካንተ ጋር ስሆን / Kante gar sihon /Endalkachew Hawaz & Heldana Shebabaw with Halwot Worship Band
Пікірлер: 35