#subscribe #subscribe #orthodox
እናት አለኝ የምታብስ እንባ #orthodox #Mezmur # • ኪዳነ ምህረት(፪)አምባ መጠጊያ ናት...
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
#ኪዳነምህረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
ራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጏ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነምህረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ..........
ለዘላለም ንፅሕት በመሆኗ
ከእኔ ጋር ነው ሕያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሐዘኔን አልፌ
አፅናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
ኪዳነምህረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ.........
ከጥፋት ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በሕይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ
ኪዳነምህረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ.........
በእናትነት ሕይወቴን ጎብኝታ
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ
ሰንሰለቴ ከእግሬ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ
ኪዳነምረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ.........
ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
ራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጏ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነምህረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
Негізгі бет Ойын-сауық ኪዳነ ምህረት(፪)አምባ መጠጊያ ናት /*አያታለሁ ስወጣ ስገባ/ኪዳነምህረት አምባ መጠጊያ ናት
Пікірлер: 1