ለካ ምህረትህ ነው
በቃልኪዳን (ሊሊ) ጥላሁን
Leka Mihretih new
By singer Kalkidan (Lili) Tilahun
Album 5
Lyrics
ለካ ምህረትህ ነው የሚደጋግፈኝ
ለካ ይቅርታህ ነው እኔን የሚያቆመኝ
ለካ ፍቅርህ ነው የሚያጠነክረኝ
ለካ ክብርህ ነው ውበት የሚሆነኝ
ከወርቅ ከዕንቁ ይልቅ ጌታ ይሻለኛል
ማለዳ ማለዳ ምህረት ያጠግበኛል (2x)
ማለዳ ማለዳ ሠላም ያሰጠኛል
ማለዳ ማለዳ ፍቅር ያጠግበኛል
ማለዳ ማለዳ ጤና ያሰጠኛል
በምን ቃል ልናገር በምን ቋንቋ ላውራ
ከአይምሮ በላይ ነው ጌታ የአንተ ሥራ (2x)
ብዙ ብዙ ብዙ ብዙም ሚለው ቃል ከገለጸው
የፍቅርን ብዛት ብዙ ነው ብዬ እናገራለሁ
ብዙ ብዙ ብዙ ብዙም ሚለው ቃል ከገለጠው
የስጦታን ብዛት ብዙ ነው ብዬ እናገራለሁ
ለካ ምህረትህ ነው የሚደጋግፈኝ
ለካ ይቅርታህ ነው እኔን የሚያቆመኝ
ለካ ፍቅርህ ነው የሚያጠነክረኝ
ለካ ክብርህ ነው ውበት የሚሆነኝ
ከወርቅ ከዕንቁ ይልቅ ጌታ ይሻለኛል
ማለዳ ማለዳ ምህረት ያጠግበኛል (2x)
ማለዳ ማለዳ ደስታ ያሰጠኛል
በምን ቃል ልናገር በምን ቋንቋ ላውራ
ከአይምሮ በላይ ነው ጌታ የአንተ ሥራ (2x)
ብዙ ብዙ ብዙ ብዙም ሚለው ቃል ከገለጸው
የፍቅርን ብዛት ብዙ ነው ብዬ እናገራለሁ
ብዙ ብዙ ብዙ ብዙም ሚለው ቃል ከገለጠው
የይቅርታን ብዛት ብዙ ነው ብዬ እናገራለሁ
Негізгі бет ለካ ምህረትህ ነው በቃልኪዳን (ሊሊ) ጥላሁን || Leka Mihretih new By singer Kalkidan (Lili) Tilahun
Пікірлер: 19