መልክአ ቅዱስ ራጉኤል_*
1. እጼውእ ስመከ፦
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል ሆይ ስምህን ጠርቼ እጅ እነሣለሁ የጥንት ጠላት የዲያብሎስን ግብር የምትጠላ ሊቀ ብረሃናት ቅዱስ ራጉኤል ሆይ መዓልት ከእለፈ በኋላ በጨለማ ጌዜ በሰማይ ጠፈር መካከል የሚመላለሱ ጨረቃ እና ከዋክብት ለቃልህ ሥልጣን ይታዘዛሉ ።
2. ለፊደለ ስምከ፦
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል ሆይ ስም እጠራሩ የአማረና በሄኖክ መጽሐፍ አስቀድሞ ለተጻፈ ለስምህ ፊደል ሰላምታ ይገባል የመስንቆ ልቤ የመዝሙሩ ቃል ቅዱስ ራጉኤል ሆይ የባርያህን መታሰቢያ ጠላት ሊያጠፋ ቢመክር አቤቱ ምክሩን ለውጥ ።
3. ለኁልቈ ሥዕርትከ፦
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል ሆይ ከመነቀልና ከመላጨት ነጻ የሆኑ ለእያንዳንዱ እጅ በመንሣት ለጠጉርህ ቁጥር ሰላምታ ይገባል የፍጹም ምስጋና ምንጭ ሊቀ ብረሃናት ቅዱስ ራጉኤል ምስጋናየን በምስጋናህ ጨምረው የምለምንህ እኔን እሺ ከማለት አትዝግይ።
*🤲የቅዱስ ራጉኤል በረከት ረድኤት ይደርብን አማላጅነቱ አይለየን አሜን ፫🕯
Негізгі бет መልክአ ቅዱስ ራጉኤል melca Kidus Raguel
No video
Пікірлер: 14