ማርያም ማርያም እላታለሁ - በዘማሪ ሊቀ ዲያቆን ደሳለኝ አዲስ
በልዩ ተመስጦ የተዘመረ ድንቅ የእመቤታችን የምስጋና መዝሙር
የመዝሙሩ ግጥም
✞ማርያም ማርያም እላታለሁ✞
ማርያም ማርያም እላታለሁ
በዘመኔ ሁሉ ስሟን እጠራለሁ
እናቴ ናት ለዘለዓለም
በእርሷስ አላፍርም /፪/
ጉድለቴን ብትሞላ የቤቴን ማድጋ
ደርሳ ብታወጣኝ ከችግር መንጋጋ
አልጠግብ አልኩኝ ስሟን ተመግቤ
ማርያም/፪/ ሆነ የሕይወት ቀለቤ
አዝ•••
ልክ እንደ ብህንሳው አባ ህርያቆስ
ያልቃኘሁት የለም እሷን ለማወደስ
በጠባብ አዕምሮ ስላልተሰፈረ
ንዒ/፪/ አልኩኝ ፍቅሯ እየጨመረ
አዝ•••
እድሜዬን በሙሉ አልጨርሰው ብዬ
ወደ ላይ ተጓዝኩኝ ሆና መሰንቆዬ
የሙሴ ምስጋና አጸደ መቅደሱ
እርሷ ናት ለያሬድ ቅኔ መወድሱ
አዝ•••
ሞገስ ለብሻለሁ በባዕድ ከተማ
መጎናጸፊያዬ ሆኖኝ የአንቺ ዜማ
ፍርሐቴን ወርውሬ ስድቤንም ረግጬ
ባልተመቸኝ ስፍራ ጠራሁሽ አብልጬ
አዝ•••
ማርያም ማርያም እላታለሁ
በዘመኔ ሁሉ ስሟን እጠራለሁ
እናቴ ናት ለዘለዓለም
በእርሷስ አላፍርም/፪/
Негізгі бет ማርያም ማርያም እላታለሁ - በዘማሪ ሊቀ ዲያቆን ደሳለኝ አዲስ [Mariam Mariam Elatalehu]
Пікірлер: 39