ናና የምስጋና ጌታ ናና የምህረት ጌታ
ማዳንህ ተገኝታለችና ሰላምህ ተገኝታለችና
ኢየሩሳሌም ሆይ ምስጋናን ክምር
መለከትን ንፊ ነጋሪት ጎስሚ
ሰላምሽ ታውጇል መዳንሽም ቀርቧል
ጌታ ሊጎበኝሽ ከበራፍሽ ቆሟል
ያልታደልሽው ሀገር ጌርጌስዮን ሆይ
ለምን ተቃወምሽው አምላክሽን ስታዪው
የከተማውን በር መዝጊያውን ቆልፈሽ
ከሩቅ የሸኘሽው ሲመጣ ሰላምሽ
የቢታንያ ድንጋይ አንደበት አውጥቶ
ምስጋና ጀመረ አምላኩን ለይቶ
ሳርና ቅጠሉ ዘንባባው ሰገደ
ፍጥረት ሊያመሰግን አምላኩን ወደደ
ህፃን ሽማግሎ ምስጋና ሲያቀርቡ
ተቆልፎ ነበር ፈሪሳዊው ልቡ
ዛሬም ለምስጋና ልባችን ይለወጥ
ሆሳህና ጌታ ይመላለስበት
Негізгі бет ናና የምስጋና ጌታ ናና የምህረት ጌታ | nana yemisgana geta nana yemkihiret geta | የክራር ዝማሬ | @zmare_yared
Пікірлер: 13