ቅዱስ ገብርኤል
ቅዱስ ገብርኤል
በሰማይ መላእክትን እንጽና ያልካቸው
ወንጌል ብረሃንን አንተ ሰበካቻው(2)
ዜናን የምታደርስ ከላይ ከአምላካቸው
ገብርኤል አንተ ነህ አጽናኝ ብርታታቸው(2)
ሔዋን ስታለቅስ ፈጣሪን በድላ
ማርያምን አብሥረህ የሰጠሃት ተድላ
እኛም ስንጠራህ ገብርኤል ቶሎና
ስምህ በእግዚአብሔር ክብርአለውና(2)
------------------
ለሠለስቱ ደቂቅ በእምነታቸው ጽናት
ፈጥነህ የደረስክ እሳቱን ለማጥፋት
ናቡከደነፆር በእሳት ውስጥ ስላየህ
ጣኦታትን ነቅሎ አንተን ተከተለህ(2)
-----------------
ቂርቆስ ኢየሉጣን ንጉሥ ፈርዶባቸው
ክብረቱ ጋን ውስጥ ወስዶ ሲጥላቸው
ከእግዚአብሔር ተልከህ አንተ ዋስ ሆንካቸው
ያን ታላቅ ነበልባል አጠፍህላቸው(2)
-----------------
ለቁጣም ለምሕረት የምትላክ መልአክ
ምሕረትን አምጣልን ሕዝቦችህንም ባርክ
ዛሬም እንጮሃለን ስምህን በመጥራት
ፍቅርና ሰላምን ለኢትዮጵያ አብሥራት(2)
#mahadev #donkey #habesha #mahtot_tube #eotc #ለእውነት #መዝሙር #mezmur #ebs @-mahtot @comedianeshetu @MKStudioIN @-betaqene4118 @quanquayeneshmedia4055 @አቤልበገና2 @beterama. @agapezeortodox @zemarideaconsamsonnegash5941 @-zemawetibebzmk7905 @meskeremwolde2826 @zemariferazerdesalegn4343 @zemarit_hewan_tube @kinetzehiyaw9688
-------------------------
Негізгі бет ቅዱስ ገብርኤል ዘማሪ ዲ/አብረሃም ደግፉ እና በዘማሪት ብርቱካን ገደፋው 18/11 16ግጥምና ዜማ በዘማሪ ዲ/ን አብረሃም ደግፉ እና በዘማሪት ብርቱካን ገደፋው
Пікірлер: 40