ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም?
ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም
ጾሙ ምን ጎደለው ?
ካአባቶቻችን እንደሰማነው እንደተማርነው
ከትውፊቱ ከመጻህፍቱ እንዳነበብነው ... እየጾምን ነው
በነብያት በሐዋርያት እንደተሰበክነው
በቆረንቶስ ገዳም ስትጾም እንዳየነው... እየጾምን ነው
ታዲያ ...
ዋጋችን የት አለ ? ጾሙ ምን ጎደለው ?**
ፊትህን ለማየት ወድቆ በጾም ጸሎት
ማነው ያልከበረ ምህረትህ ደርሶት
በቃልህ መጽሐፍ ተጽፎ ያየናቸው
ክንድህን አይተዋል ዋጋ አለው ጾማቸው
የኛ ምን ጎድሎት ነው ስንጾም የማታየን
እንደ ኤልዛቤል ጾም ፣ ስለምን ተቆጠርን ?
አዝ ...
ሙሴ በጾመ ቀን አርባ ሌትና መአልት
ሰጠህው ህግህን የድንጋዮን ጽላት
በእሳት ነበልባል ቀርበህ አነጋገርከው
ምን ብንበድልህ ነው ድምጽህን ያራከው ?
ጾማችን ምን ጎድሎት እራቀን ምረትህ
ፍጹም አይደለንም ይፍረድልን ፍቅርህ
አዝ ...
በሱሳ የነበሩ አይሁዶች በሙሉ
ሦስት ቀን ቢጾሙ ይቅር በለን ቢሉ
የሃማን ቤት ወስደህ ለአስቴር ሰጠህው
የንጉሡን አዋጅ ሞቱን ገለበጥከው
የኛ ምን ጎድሎት ነው ስንጾም የማታየን.
እንደ ኤልዛቤል ጾም ስለምን ተቆጠርን ?
አዝ ...
የነነዌ ሰዎች ማዳንህን አዮት
የመጣውን ቁጣ እሳቱን መለሱት
ምህረት አወረደ ጾማቸው ከሰማይ
መቼ ነው ጾማችን ባንተ ፊት የሚታይ
መልስ ሲቀበሉ እነሱ በሦስት ቀን
ጾሙ ምን ጎድሎት ነው ዘመናት ያለፈን ?
አዝ ...
በኢየሩሳሌም በጾም ጸሎት ሆነው
አንዲት ልብና ነፍስ፣ አንዲት ሃሳብ ሆነው
ጾመው ሲጸልዮ የወረድከው መንፈስ
ልባችንን ቀይር ጾማችን ይቀደስ
ቀድሱት ያልከንን ጾምን እስክንቀድስ
ፍቅርህ ይራራልን ምድራችንን ፈውስ
ዘማሪት እሌኒ ደስታ
ግጥም ዲያቆን መኩሪያ ጉግሣ
ዜማ ዘውዱ ጌታቸው
ክራር :- ዘውዱ ጌታቸው
ዋሽንት :- ኤልያስ ፍቃዱ
መሰንቆ :- እንዳልካቸው አዱኛ
ስቱድዮ :- ዘጎላ ስቱድዮ
Негізгі бет ጾሙ ምን ጎደለው ዘማሪት እሌኒ ደስታ ግጥም ዲያቆን መኩሪያ ጉግሣ ዜማ ዘውዱ ጌታቸው
Пікірлер: 50