ሊቀ መልአክ ዑራኤል አባት
ፀበልህም ያድናል በእውነት
በምልጃህም ያመኑ በሙሉ ባንተ ይድናሉ
ዑራኤል መልአክ ማዳንህን ሰምቼ
ዑራኤ መልአክ ስምህን ጠርቻለው
ዑራኤል " አላሳፈርከኝም
ዑራኤል " ባንተ ኮርቻለው
ዑራኤል " መንገዴ ባንተ ነው
ዑራኤል " የኔ መታመኛ
እኔንም ጠብቀኝ ከሀጢአት ቁራኛ
አዝ................
ዑራኤል መልአክ ያንተ ድንቅ ሥራ
ዑራኤል መልአክ አይመረመርም
ዑራኤል መልአክ ድንቅ ነው ምህረትህ
ዑራኤል መልአክ ማዳንህ ዘላለም
ዑራኤል መልአክ ቸርነትህ ብዙ
ዑራኤል መልአክ ምልጃህም ፈጣን ነው
ፀጋህን ላክልን ለእኛ ለምናምነው
አዝ........................
ዑራኤል መልአክ ለእዝራ ስቱኤል
ዑራኤል መልአክ ጥበብ እንዳጠጣህ
ዑራኤል መልአክ በጽዋህ በረከት
ዑራኤል መልአክ ደምን እንደረጨህ
ዑራኤል መልአክ ሠላምን ልታስገኝ
ዑራኤል መልአክ ዓለመን መዞርህ
ማዳንህ ተገልጿል በቅዱስ ፀበልህ
Негізгі бет Ойын-сауық ዑራኤል አባት
Пікірлер: 2