አይናችን ነሽ ማርያም አንቺን አይንኩብን
የተዋህዶ ልጆች እንወድሻለን
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
በሀሴት ቆመናል ደስታን ስለወለድሽ
አዝ...
የቀደመው እባብ እጅግ ተበሳጨ
በአሸዋ ላይ ቆመ መርዙን እየረጨ
ከልጅሽ ምስክር ሊያስቀር ከዘሮችሽ
እጅጉን ይተጋል ሊለየን ከጉያሽ
አዝ...
ገብተሻል አትወጪም አንዴ ከልባችን
ጌታን ያየንብሽ ስለሆንሽ አይናችን
የራቀው ቀርቦልን የረቀቀው ጎልቶ
ያየነው ባንቺ ነው የጠፋው ተገኝቶ
አዝ...
ወይኑን ያፈራሽው የወይን ሀረግ ድንግል
ምግብን የሰጠሽን በቀራንዮ መስቀል
ምልክታችን ነሽ የኛ መታወቂያ
የምንተርፍብሽ ከጥፋት ገበያ
አዝ...
የህይወት መገኛ የደስታ መፍሰሻ
ፀዋሪተ ፍሬ የሃዘናችን መርሻ
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
የጎደለው ሁሉ ይሞላል በምልጃሽ
አዝ...
ከሀገር ብንርቅ ከእልፍኝ ከጉዋዳችን
ስንቅ ነሽ ለመንገድ ምርኩዝ ለጉዟችን
በአደርንበት አድረሽ በሄድንበት ሂጂ
ለፃድቃን አይደለም ለሃጢያን አማልጂ
Негізгі бет አይናችን ነሽ ማርያም በክራር ሲደረደር | Aynachn Nesh Mariam | Kirar turorial
Пікірлер: 19