ሙሽራው ሙሽርት
ከበሩ በእግዚአብሔር ፊት
ያማረ በፍታ ለብሰዋል
በከፍታላይ ቆመዋል
አምላክ በፍቅር ያፅናችሁ
ወልዶ ለመሳም ያብቃችሁ
ሙሽራው ያበራል ፀዳሉ ሙሽሪት ያበራል ፀዳሏ
አገኘ የጎን አጥንቱን
አገኘች እርሳም ህይወቷን
አንድ ሆነዋል ዛሬ ሁለቱ
በቅድስናው በቤቱ
ሙሽራው ፀዳሉ ሙሽሪት ያበራል ፀዳሏ
በከበረው ከብረው
ይህው ታዮ ደምቀው
ይታወጅ ይሄ ደስታ
እንዘምር በእልልታ
ሙሽራው ያበራል ፀዳሉ ሙሽሪት ያበራል ፀዳሏ
የእናት የአባት ምርቃት
ይህው ለዚህ በቃ ለዚህ ዕለት
ባረኩት ይህው ህብስቱን
ከፍ አድርገው ፅዋውን
ሙሽራው ያበራል ፀዳሉ ሙሽሪት ያበራል ፀዳሏ
Негізгі бет የሠርግ መዝሙር በዘማሪ ብርሃኑ ተረፈ ጽፋት (የህብስት ማስቆረሻ ከዘማሪት አዜብ ጋር የዘመርነው ቤተሰብ ይሁኑ ሼር ያድርጉ
Пікірлер: 2