የዛሬው መጻፍ The Power of Positive Thinking or የአዎንታዊ አስተሳሰብ ሃይል የሚባል ነው። በ Dr ኖርማን ቪንሰንት ፔሌ የጻፈ ነው። ደራሲው የአሜሪካን ሃገር ፓስተር ወይም ሰባኪ ነው ያማለት በጣም ነው መጻፍ ቅዱስ ላይ የሚያቶክረው። ደራሲው የቀና አስተሳሰብን ጽንሰ ሃሳቦችን አጋኖ በማሳወቅ እንዲወደድ በማድረግ የተዋጣለት ጸሃፊ ነው። የሚለን ምንድነው አወንታዊ ተቀጽላዎችን ለራሳችን መናገር ብቻ አይበቃም ከቅዱስ መጻፍ ጥቅሶች ጋር ማደባለቅ አለብን ይለናል። አክሎም ቅዱስ መጻፍ ላይ ያሉ ጥቅሶች ለሰዎች የተሰጡ ቃልኪዳኖች ናቸው እና መጠቀም አለብን ይለናል። ለምን ብትሉ የሃሳብ ብቻ ሳይሆን የመንፈስን ሰላቢዎችን ለመከላከል ይለናል። በአሉታዊነት ካሰቡ አሉታዊ ውጤቶችን ያገኛሉ ፡፡ በአዎንታዊ ካሰቡ ግን ሕይወትዎ የተሻለ እና አዎንታዊ ይሆናል። ቀና አመለካከት ያላቸው ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ መልካም ነገሮች እንደሚከሰቱ ስለሚጠብቁ የበለጠ እርካታ ያለው ሕይወት አላቸው ፡፡ ስለሆነም ፣ አስተሳሰባችን በአዎንታዊ እና በተስፋ የተሞላ እንዲሆን ከለወጥን, ታላላቅ ነገሮችን ማሳካት እንችላለን ነው የሚለን።
Негізгі бет የአዎንታዊ (የቅን) አስተሳሰብ ሃይል
Пікірлер: 74