#engedachn #graceworship #helinadawit #minasefirdawek #mezmur #gospelsong #liveworship #amharicworship
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:35
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?
Grace Worship
Facebook: @graceworship01
Instagram: @graceworship01
Telegram: +251920810703
Call: +251912760494
Lyrics
እንግዳችን ቤተኛችን አለኝታችን
ለሰው ሁሉ የምናሳይህ ልዩነታችን
ዛሬ ደግሞ በተለየ ተናፍቀሀል
እኛ ቤት ላንተ ሲሆን ምንም ይደረጋል
እኛ ቤት ላንተ ሲሆን ምንም ይዘጋጃል
ከእልፍ የተመረጥክ በውበትህ
መታመኛ የሆንክ ለቤትህ
ሸክሙ ለከበደ ማረፊያ
የዘላለም ጥላ መኖርያ
ከያለንበት ሰበሰብከን
በደምህ አጥበህ አፀደከን
ዛሬማ ማን ይቃወመናል
እንድናጥንልህ ሆነናል
ብርቱዎችን እንድታሳፍር
በደካሞች ልትከብር ወደሀል
በምህረትህ ግብዣ ታድመን
ወደንህ አንተ ጋ ቀርተናል
ዛሬም አንተ ነህ ጥማታችን
እንድናይህ ነው ጉጉታችን
በክብረለር ዳግም ተመልሰህ
እስክትወስደን ወደ ቤታችን
ከፍታ ቢሆን ዝቅታ
ሀዘንና ብዙ ደስታ
ባርነት ወይስ ነፃነት
መላዕክት ወይ ልዩ ፍጥረት
የቱ ነው የቱ በረከት ሚለየን
ከፍቅርህ ጉልበት
የቱ ነው የቱ ከፍታ ሚለየን ከፍቅርህ ጌታ
ትበልጥብናለህ/x4/
የተመኘነው ባይሞላ ያሰብነው ቢሆንብን ሌላ
ትበልጥብናለህ
ልታድነን ትችላለህ ባይሆንም ግን አባታችን ነህ
ትበልጥብናለህ
Негізгі бет ልዩነታችን || Liyunetachin || Engedachn ||Grace Worship || New Music Video 2022 Official
No video
Пікірлер: 740