👇🏼ለዐቢይ ጾም ሳምንታት የተዘጋጁ👇🏼
• 🛑 ዘወረደ 🛑 የጥበብ ሥራ || የን...
• 🛑 ቅድስት 🛑 ጾምን ቀድሱ || የን...
• 🛑 ምኲራብ 🛑 ለመልካም ኾነልኝ ||...
• 🛑 መጻጕዕ 🛑 ሰው የለኝም አትበል ...
• 🛑 ደብረ ዘይት 🛑 እንዳያስቷችኹ |...
• 🛑 ገብርኄር 🛑 ታማኝ ልኹን || የ...
• 🛑 ኒቆዲሞስ 🛑 ይህ እንግዳ ማነው?...
• 🛑ሆሣዕና🛑 ይበል ይበል || የንስሓ...
👇🏼የመዝሙሩ ሙሉ ዘር👇🏼
🛑 የጥበብ ሥራ 🛑
መግቢያ
እንደ ጠቢብ ሰው ኹን ክርስቲያን ሆይ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ኩኑ እንከ ከመ ብእሲ ጠቢብ
(ትርጉም፦ ሃሌ ሉያ ፤ እንግዲህ እንደ ጠቢብ ኹኑ)
የትሩፋት ኹሉ እናታቸው ናት
ጾም ትፈውሳለች ከትዕቢት ቁስለት
የጌታን መከራ የሰማዕታትን ግፍ ኃጢአቷን ዐስባ
ነፍስኽ ቢያቅታት ማልቀስ በጽድቅ ዕንባ
ጾም ናት መድኃኒትኽ ወደ እልፍኟ ግባ
- - - - - - - - - - - +++ - - - - - - - - - - -
እንደ ጠቢብ ሰው ኹን ክርስቲያን ሆይ
ጾምን እንደሚወድ እንደሚጸልይ
በንጹሕ ልቡና ጌታን እንደሚያይ
እንደ ጠቢብ ሰው ኹን ክርስቲያን ሆይ
- - - - - - - - - - - +++ - - - - - - - - - - -
የጎደለን አለ ያላገኘኘው
ብለን ብቻ ነው ወይ የምንለምነው
ለጸሎት ከፊቱ እንቁም ሲጨላልም ብርሃኑም ሳለ
ከምድሩ ምቾት ከኹሉ ያየለ
የሰማዩ አባት የሚሰጠን አለ
- - - - - - - - - - - +++ - - - - - - - - - - -
እንደ ጠቢብ ሰው ኹን ክርስቲያን ሆይ
ጾምን እንደሚወድ እንደሚጸልይ
በንጹሕ ልቡና ጌታን እንደሚያይ
እንደ ጠቢብ ሰው ኹን ክርስቲያን ሆይ
- - - - - - - - - - - +++ - - - - - - - - - - -
ሰውነታችንን ከሚበጣጥሳት
ከማይቆራረጥ ከየዕለት ኃጢአት
መዳን ለምንሻ ፣ የመንግሥተ ሰማይ መንገድ የምትመራ
ለጌታ ኾነች ሥራ መጀመሪያ
የምኞት ጠላት ጾም የጥበብ ሥራ
- - - - - - - - - - - +++ - - - - - - - - - - -
እንደ ጠቢብ ሰው ኹን ክርስቲያን ሆይ
ጾምን እንደሚወድ እንደሚጸልይ
በንጹሕ ልቡና ጌታን እንደሚያይ
እንደ ጠቢብ ሰው ኹን ክርስቲያን ሆይ
- - - - - - - - - - - +++ - - - - - - - - - - -
ሑሩ በጽድቅ ትርከቡ ሠናየ ሑሩ በጽድቅ ትርከቡ ሠናየ
(ትርጉም፦ መልካም ነገርን እንድታገኙ በእውነት ኺዱ)
👇🏼ይወዳጁን👇🏼
t.me/Lisanesurafi
www.tiktok.com/@lisanesurafi?...
/ lisane_sura. .
/ h8r9cn. .
#mezmur #newvideo #ethiopianmusic #ethiopianorthodoxtewahedochurch #viral #viralvideo
Негізгі бет 🛑 ዘወረደ 🛑 የጥበብ ሥራ || የንስሓ መዝሙር በጸጋ ሥላሴ (ዲ.ን) I New Mezmur By Tsegasilase I
Пікірлер: 51