እግዚአብሔርን አመስግኑ
===================
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት / 2 /
አ.ዝ-----------------------//
ሰማይን ያለ ምሰሶ
ምድርንም ያለ መሠረት
ያጸናው እርሱ ነው
ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት / 2 /
አ.ዝ-----------------------//
የባሕርን ጥልቀት የመዘነ
ዳርቻውን የወሰነ
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት / 2 /
አ.ዝ-----------------------//
ማዕበል ነፋስን የሚገስጽ
ፍጥረቱ ለስሙ የሚታዘዝ
ትጉህ እረኛ ድካም የሌለበት
እግዚአብሔርን ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት / 2 /
አ.ዝ-----------------------//
ንጹሐ ባሕርይ ነው ሁሉን የሚገዛ
የነገሥታት ንጉሥ አልፋና ኦሜጋ
ዘለዓለም እርሱ የማይለወጥ
እግዚአብሔርን ስራህ ድንቅ ነው በሉት
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት / 2 /
አ.ዝ-----------------------//
ጥበብን የሚገልጽ ጥበበኛ
ፍርድ የሚያደርግ እውነተኛ ዳኛ
እንደ እርሱ ያለ ከቶ አይገኝም
እግዚአብሔር ግሩም ነው ዘለዓለም
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት / 2 /
Негізгі бет እግዚአብሔርን አመስግኑት ስራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት
Пікірлер: 83