HUA-ኋ
ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን በያላችሁበት ሰላም ሁኑልኝ። በእርግጠኝነት ይሄንን የዩትዩብ ቻናሌን መግለጭያ ፅሁፍ የሚያነብ ይኖራል ለማለት ይከብዳል። ቢሆንም ግን ይሄንን ፅሁፍ መፃፌ አስፈላጊነቱ ቻናሌን ብቅ ብለው አይተው ወደ ውስጥ ለሚመለከቱ ኢትዮጵያውያን መልስ ይሆናል ብየ ስለማስብ ነው።በመጀመሪያ ደረጃ እኔ ዮኋንስ እባላለሁ። ወደ ቻናሉ ስያሜ ስንመጣ ደግሞ፤ የቻናሉ ስም “ኋ’’ ይሰኛል በቃ እረፉት በአማርኛ አንድ ቃል ብቻ ነው። ነገር ግን በድምፁ ብቻ ወደ እንግሊዝኛ ስንቀይረው ሶስት ቃል ይሆናል ማለትም HUA ምንም እንኳ የቻይና ስም ቢመስልም። እንደምታውቁት ‘ኋ’ የምትለዋን ቃል በተደጋጋሚ የምናውቃት የኔን ስም ሰምተን ሳይሆን 'በኋላ' ከሚለው ቃል ነው። እና እኔም ቪድዮውን የማብራራላችሁ እኔ ዋና ቪድዮውን ካየሁት በኋላ ነው ለማለት ነው። አሁን አንብባችሁት ብትስቁም ሳቁ ይመቻችሁ ትርጉሙ ቀላል ቢሆንም ባልነራችሁ የት ታመጡት ነበር።
በዚህ ቻናል ላይ የሚተነተኑ ቪድዮዎች
የተመረጡ የሀገራችን የሙዚቃ ስራዎች
ከሙዚቃ ውጭ ያሉ የተመረጡ ቪድዮዎችን
አስገራሚ እና አስተማሪ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተሰሩ ቪድዮዎችን ተርጉሜ የማቀርብላችሁ ይሆናል
ቪድዮዎቼን በየሳምንቱ ቅዳሜ ምሽት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር 2፡00 ላይ ያገኟቸዋል። አስቀድሞ እንዲደርሳችሁ SUBSCRIBE አድርጉ እናም የደወል ምልክቷን ይንኩ። ቪድዮው ከተመቻችሁ LIKE ማድረጋችሁን እንዳትረሱ ላይክ በማድረጋችሁም ከብዙ ተመልካች አይን ውስጥ እንድገባ ያደርገኛል። አስተያየት ካላችሁም ሜዳው የናንተ ነው ፈታ በሉበት። ነገር ግን ይሄን ቪድዮ እየውና አስተያየት ስጥበት ካላችሁ ደግሞ ሊንኩን አስቀምጡልኝ በምችለው መልኩ እናም መርጨ የማቀርበው ይሆናል። መልካም ጊዜ።
#HUA #ኋ
- 14:23
- 3 жыл бұрын
Пікірлер