አጋጣሚ አይደለም መትረፌ መዳኔ
የጌታ ተአምር ነው እረ ይገርማል የእኔ
ሞት እንቅልፍ ሆነልኝ ጭንቀቴ ቀለለ
የረዳኝ ጌታ ነው ውዴ እየተከተለ
አዝ...
ማን ነው በዛ በረሃ ያበላኝ መና ያጠጣኝ ውሃ
ማን ነው የደገፈኝ ጥልቁን ሸለቆ ያሻገረኝ
አንተ ነህ ለእኔ እናት አባቴ
ንጹህ ወዳጄ ስጋ እና አጥንቴ
አይኔ አይነቀል ከዙፋንህ
ፊት አያዞርም ፍቅር አይንህ
አዝ...
ወሮኝ ድቅድቅ ጨለማ
ተስፋዬ ከስሞ ልቤ ሲደማ
አይቶኝ ሲፈስ እንባዬ
ደመና ጠቅሶ መጣ ጌታዬ
ፀሀይ ነው እና የብርሃን አምዴ
ኢየሱስ ለእኔ ህይወት መንገዴ
አልተሸነፍኩም ውዴ አግዞኛል
መቃብር ከፍሎ ህይወት ሰጥቶኛል
አዝ...
ሲለይ ነፍሴ ከስጋ በጨለማ ቀን በክፉ አደጋ
ዳንኩኝ ሞት እያየኝ የንሰሃ እድሜ ጨመረልኝ
በጽድቄ አይደለም የተረፍኩት
በእሱ ፍቅር ነው በእሱ ምህረት
ብቻዬን ሆኘ ሁሌ የማለቅሰው
እየበደልኩት ስላዳነኝ ነው
አዝ...
ሞት ሆይ መውጊያ የታለ
ብሎ ጥሎኃል እየታገለ
ሲኦል ድል መግዛትህ
ባዶ ቀርተሃል ተበዝብዘህ
በእራሱ መንግስት ፈጥሮኝ በዓላማ
የልጁን ህይወት ማንም አይቀማ
መቃብር ያርፋል በአገልግሎቴ
ተከፍቶልኛል ደጁ የአባቴ
አዝ...
ታምር ነው
for more mezmur and perching
www.mulakonjo.b...
www.arsemaenat....
Негізгі бет Музыка ethiopian orthodox mezmur by abel agatami aydelem with lyrics
Пікірлер: 15