#ፃድቁ_አቡነ_ሐብተ_ማርያም
☞•••ግንቦት 26 እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የልደት በዓላቸውበሰላም አደረሳችሁ፡፡
☞አባታቸው ፍሬ ቡሩክ እናታቸው ዮስቴና የሚባሉ በሕገ እግዚአብሔር፡ በሃይማኖት በምግባር ጸንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች የገኙ አባት ናቸው፡፡
☞አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም ፅንሰታቸው ነሐሴ 26፤ ውልደታቸው ግንቦት26፤ ዕረፍታቸው ኅዳር 26 ነው፡፡
☞አቡነ ተክለሃይማኖት አቡነ ሀብተማርያምን አምስት መቅሰፍታት እንዲጠፋ በደጄ በደብረ ሊባኖስ ተቀበርልኝ ብለው የለመኗቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ይህ እንዴት ነው ቢሉ☞አቡነ ተክለሃይማኖት እኔ ከተቀበርኩበት ቦታ እድትቀበር ቃልኪዳን ግባልኝ ብለው ጠየቋቸው፡፡
☞አቡነ ሀብተማርያምም አባቴ ሆይ ይህንን አደርግ ዘንድ ሰለምን ትወዳለህ? አላቸወ፡፡ ☞አቡነ ተክለሃይማኖትም በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስት መቅስፍቶች አሉና
ሰለዚህ ነው እነዚህም አንዱ መብረቅ ሁለተኛው ቸነፈር ነው ሦስተኛው ረሀብ ነው፤ አራተኛው ወረርሽኝ ነው አምስተኛው የእሳት ቃጠሎ ነው፡፡ የአንተ አጽም በውስጡ የተቀበረ እንደሆነ ከነዚህ መቅስፍታት ትድናለች አሏቸው፡፡
☞አቡነ ሀብተ ማርያም ንዑድ ክቡድ የምትሆን አባቴ ሆይ ልዩ ክብር በሚሆን በአንተ አጽም መቀበር ያልዳነች በእኔ አጽም መቀበር ድኅነትን ታገኛለችን? ብለው ተከራከሩ በዚህም ጊዜ አቡነ ተክለሃይማኖት መልሰው ☞አንተ የማታውቀው ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሔር የተሰጠህ እኔ የማውቀው ክብር አለህና ሰለዚህ ነው፡፡ ይልቅስ እንዳልኩህ በተቀበርኩበት ቦታ እንድቀበር ቃልኪን ግባልኝ ብለው ማለዷቸው፡፡
☞ይህንንም ሲባባሉ እንዲህ የሚል ቃል መጣላቸው ከወዳጄ ከሀብተ ማርያም እንደበት ይህ ቃል አይወጣም፤ ዳግመኛም ወዳጄ ተክለሃይማኖት ሆይ እርሱ
በወደደው የሚቀበር አይደለምንና እኔ ከተቀበሩኩበት እንድትቀበር ብለህ የምታስገድደው ለምንድ ነው?
☞እኔ በወደድሁት ቦታ ይቀበራል እንጂ የሚል ቃል ተነገረ፡፡
☞አቡነ ተክለሃይማኖትንም እየለመኑና እየሰገዱከሥላሴ ዙፋን ተንበረከኩ፡፡☞በሦስተኛውም ይሁን እንዳልከው ይቀበርልህ የሚል ቃል ተሰማ፡፡ ☞ዳግመኛ በአንተም አጽም በሀብተ ማርያምም አጽም ቦታህ ከመቅሰፍት
ትድናለህ ልጆችህ ግን በቸነፈር ደዌ ቢሞቱ ከሰማዕትነት ተቆጥሮላቸው ወደ መንግሥት ሰማያት እንዲገቡ በራሴ ምዬ ቃልኪን ገብቼለሃለሁ አላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ አቡነ ተክለሃይማኖት እጅግ ደስ ተሰኙ፡፡
☞(ገድለ አቡነ ሀብተማርያም)
Негізгі бет ገድለ አቡነ ሀብተማርያም (አርብ የሚነበብ)// 5ቱን መቅሰፍታት በተሰጣቸው ልዩ ቃልኪዳን የሚያጠፉት ቅዱስ አባት በፀሎታቸው በቃልኪዳናቸደው ይማረን ይቅር
Пікірлер: 12