በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን:: በሰማነው ልክ እንናገራለን በአየነውም ልክ እንመሰክራለን:: ነገ ያስፈራል! ግን ''እንዳናስተውል ፣እንዳንታዘዝ አዚም ያደረገብን ማነው? ወላዲተ አምላክ ሳለች ኢትዮጵያ ትፈተን ይሆናል እንጂ አትሸነፍም አስራት ሀገሯን የቢጫ ወርቅ ስጦታ የተባለችውን ኢትዮጵያ እመቤታችን አትተዋትም ልጇም አይዘነጋትም...ሁላችንም በፀሎት እንበርታ በያለንበት ወደ ፈጣሪ እጃችንን እናንሳ ልቦናችንን አጥርተን ውድ የግዜ ቲዩብ መርሀ ግብር ተከታታዮች ዛሬውኑ መልስ ያለው እንባን እናንባ:: እንደ ቅዱስ ዳዊት አቤቱ ድውይ ነኝ ና ማረኝ እንበለው ልቦናችንን ሰብረን መፍትሄያችን የሆነውን አምላክ ሀገራችን ላይ የመጣውን መአት አንተ አስወግድ እንበለው አባት ነውና አይጨክንም ስለዚህ በአንድ ልብ ሁላችንም እንዲህ እንበለው አቤቱ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ መዐትህ የራቀ ምህረት የቀረበ አባት ሆይ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ በደላችን አይሁን እንበለው ምክንያቱም ኢትዮጵያን አሟታልና:: አዎን ኢትዮጵያ ታማለች ያለ አርብ ስቅለት እሁድ ፋሲካ እንደሌለ ሁሉ ዛሬም የኢትዮጵያ ምድር መከራን ዳምኖ መከራን እያዘነበ ይገኛል ግን እናምናለን እንደመሸ አይቀርም ይነጋል ሊነጋ ሲል ይጨልማል ሆኖ ነው እንጂ ነገሩ የኢትዮጵያ ጥዋት፣ ንጋት ይመጣል
ስለምትመለከቱን አብዝቶ ደስ አለን ቪዲዮውን ሼር በማድረግ እናንተ ያገኛችሁትን እውቀት ለሌሎች አሳውቁ። በሀሳቡ ላይ አስተያየት ካሎት ይጻፉልን እናመሰግናለን፡፡ ይህ ግዜ ቲዩብ ነው ይህንን የግዜ ቲዩብ ዝግጅት ዘወትር እንዲደርሶ የመርሀ ግብራችን ቤተሰብ ይሁኑ በይነመረባችንን ይጎብኙት ሰላም ይኑረን ተስፋን አንጣ፡፡
Негізгі бет Ойын-сауық ኢትዮጵያ መከራ ውስጥ ናት አሁኑኑ መልስ ያለው እንባ ወደ ፈጣሪ
Пікірлер: 273