Gospel song by Singer Dr. LeAlem Tilahun. Lord you are above everything. Nothing I need besides you. You are the only one I need in my life.
"ለእኔስ ካንተ የሚበልጥ ወዳጅ የለኝም"
በዘማሪ ዶ/ር ለዓለም ጥላሁን
እንታነጽበት ዘንድ አቅራቢ
ወ/ም ሶካ
[ለእኔስ ካንተ የሚበልጥ ወዳጅ የለኝም
ፍቅርህ ዛሬም ትኩስ ነው በልቤ ከቶ አይበርድም] 2
[በመንፈስ ቅዱስ በልቤ የፈሰሰው
አቤቱ ፍቅርህ መተኪያ የለው] 2
ብዙ ውኆች እንኳን ሊያጠፉት አልቻሉም
ግሩም ነው ግሩም ነው ፍቅርህ አይነገርም
ለእኔስ ካንተ የሚበልጥ ……
[የብርሃን አባቴ የእኔ መመኪያ
ፍቅርህ ሁሌ አዲስ ነው ከልቤ የማይጠፋ] 2
አንተን አንተን እንጂ ማንንም አልልም
አምላኬ ጌታዬ ለእኔስ አንተ ፍቅር ነህ
ለእኔስ ካንተ የሚበልጥ ……
[የነፍሴ ጥጋብ የሕይወቴ አለኝታ
መጠጊያዬ ነህ ብሩኩ ጌታ] 2
ነፍሴን በምህረትህ አድነሃልና
የመድኃኒቴ አምላክ ይድረህ ምስጋና
ለእኔስ ካንተ የሚበልጥ ……
እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
Негізгі бет ለእኔስ ካንተ የሚበልጥ የለኝም Lenes Kante YemibelT Yelegnim በዘማሪ ዶ ር ለዓለም ጥላሁን LeAlem Tilahun
Пікірлер: 2