Singer: Lidia Anteneh
Music Arrangement : Robel Damtew
Directed by : Fikru Alemayehu
"እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ።" ኢሳ 12:4
"Praise the Lord, call upon his name, declare his doings among the people, make mention that his name is exalted." Isa 12
የሚያረካህ ነገር አንተ ምትፈልገው
ይገኝ ይሆን ብዬ ይዤ መጥቻለው
አንደበቴን ሙላው በብዙ ምስጋና
ዝማሬ እና ቅኔ ትወዳለህና
በቀን ስመላለስ ማዳንህ በትሬ
በለሊት ሆነልኝ በአፌ ላይ ዝማሬ
እንደ ንጋት ብርሃን በላዬ አብርተህ
መሰማሪያ አገኘው እረኛዬ ሆነህ
ሚገባህን ሁሉ በፊትህ ላፍስሠው
ምንም ነገር የለም 'ላንተ የማልሠዋው
ያየሁት ምህረትህ ከቃላቴ በልጧል
መላው አካላቴ ክብር ይሠጥሃል
በማዳን ብርቱ ነህ እኔን አግኝተሃል
ጠላትህ ሳለሁኝ ወደህ ቀርበኸኛል
ቀኝህ ሲያስመልጠኝ ከጠላቴ ዛቻ
እጅህ ስለያዘኝ ሆንኩኝ ያንተ ብቻ
'ሚገባህን ሁሉ በፊትህ ላፍስሠው
ምንም ነገር የለም 'ላንተ የማልሠዋው
ያየሁት ምህረትህ ከቃላቴ በልጧል
መላው እኔነቴ ክብር ይሠጥሃል
'ሚገባህን ሁሉ በፊትህ ላፍስሠው
ምንም ነገር የለም 'ላንተ የማልሠዋው
ያየሁት ምህረትህ ከቃላቴ በልጧል
መላው አካላቴ ክብር ይሠጥሃል
ድንቅ ነህ አምላኬ ድንቅ ነህ
ግሩም ነህ ኢየሱሴ ግሩም ነህ
አባት ነህ ጌታዬ አባት ነህ
መልካም ነህ ኢየሱሴ መልካም ነህ
Негізгі бет ሊዲያ አንተነህ - በፊትህ ላፍስሠው Lidia Anteneh - Befith Lafsisew 2013 / 2021
No video
Пікірлер: 179