አይን ሊያየው የማይችለው ጥልቅ ብርሃን
ማንም የማይደርስበት የክብር ዙፋን
የራቀውን የሚጣራ የቀረበን ይልቅ የሚያስመኝ
ከአድናቆት ሁሉ አልፎ እንደሞተ የሚያደርግ
መኖሪያህ ነው ልዕልና
መኖሪያህ ነው የክብር ደመና
መኖሪያህ ነው ቅድስና
መኖሪያህ ነው የመንፈስህ መገኛ
ክብር4* ማንነትህ ነው
ክብር4* መገለጫህ ነው
ክብር4* ማንነትህ ነው መገለጫህ ነው
ፅድቅን ተጎናፅፈህ ቅድስናን ተላብሰህ
በሞገስ በመፈራት ከሁሉ እጅግ አይለህ
የዘመናት ቁጥር በእጆችህ ይዘህ
አንተ ግን ያው ሆነህ ልቀህ ትኖራለህ
መኖሪያህ ነው ልዕልና
መኖሪያህ ነው የክብር ደመና
መኖሪያህ ነው ቅድስና
መኖሪያህ ነው የመንፈስህ መገኛ
ክብር4* ማንነትህ ነው
ክብር4* መገለጫህ ነው
ክብር4* ማንነትህ ነው መገለጫህ ነው
ለመንግሥትህ ፍፃሜ የለውም መጨረሻ
ዙፋንህ ፅኑ ነው መቼም ማይረታ
ለዘመንህ ማብቂያ ዳርቻ የሌለህ
አምልኮና ስግደት የተገባህ
አቤት3* ክብር
አቤት3* ሞገስ
አቤት3* ልዕልና
እንዳንተ የለም ባለግርማ
Негізгі бет Музыка መኖርያህ ነው Menoryah new አዲስ አበባ አጥቢያ የህይወት ቃል ቤ/ክ ዞዊ የመዘምራን ህብረት
Пікірлер: 24