Gospel song by singer Shewaye Damte. Jesus Christ is the same yesterday, today, and forever. All things change, but Jesus is Alive and King.
"ትላንት ከትላንትም በስቲያ"
በዘማሪ ሸዋዬ ዳምጤ
እንታነጽበት ዘንድ አቅራቢ
ወ/ም ሶካ
ዓለም መልኳን ስትቀየር
ስትሾምና ስትሽር
ኃያላን ሲሰወሩ
በሞት ባሕር ሲቀሩ
ኢየሱስ አለ በክብሩ
ትላንት ከትላንትም በስቲያ
ነገም ከዚያም ለዘለዓለም
ጌታ ኢየሱስ ሕያው ነው
እርሱ ከቶ አይለወጥም
ምድርን የበደል ብዛት
የእሳት ዲን ሲያለብሳት
ፍጥረት ሩጫውን ሲያቆም
ለዘለዓለም ሲያከትም
ኢየሱስ አይለወጥም
ትላንት ከትላንትም በስቲያ….
አማኝ ሥፍራውን ቢለቅ
በኃጢአት ቢጥለቀለቅ
በተቀደሰው ስፍራ
የጥፋት ልጅ ቢያጓራ
ኢየሱስ አለ ሲያበራ
ትላንት ከትላንትም በስቲያ…
የሚወዱት ቢከዳ
ሕይወት ቢሆን ገዳዳ
ነገር ቢሆን ተራራ
ሰይጣንም ቢያቅራራ
ጌታ ነው ከእኛ ጋራ
ትላንት ከትላንትም በስቲያ….
እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
Негізгі бет ሸዋዬ ዳምጤ Shewaye Damte ትላንት ከትላንትም በስቲያ Tilant Ketilantim Bestiya
Пікірлер: 14