ጥንታውያን ኢትዮጵያውያን አሁን ድረስ ለአለሙ ማህበረሰብ እንቆቅልሽ የሆኑ የስነ ግንባታ ውጤቶችን አበርክተዋል:: እነኚህ የአባቶቻችን የስነ ግንባታ ውጤቶች ምስጢራዊና አስደናቂ የሚያደርጋቸው አሁን ስልጣኔ በረቀቀበት በዚህ ዘመን እንኳን አለመሰራታቸው ነው ለአብነትም በተለያዩ የሀገራችን ክፍል የሚገኙትን ውቅር ስነ ህንፃዎችን ማንሳት ይቻላል:: ከዚህም በላይ አሁን ድረስ አለም ያልደረሰባቸው፣ ከማይቀረው የኢትዮጵያ ትንሳኤ ጀርባና ኢትዮጵያን አንድ ከሚያደርገው ከደጉ ንጉስ መምጣት ጋር ተያይዞ ከተሰወሩበት ቦታ የመገለጥ ግዜያቸውን እየጠበቁ ያሉ ፍፁም ምስጢራዊና አስደናቂ የፒራሚድ ከተሞች በስውር በኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛሉ........ ሰላም ይኑረን ተስፋን አንጣ ውድ የግዜ ቲዩብ መርሀግብር ተከታታዮች እንደምን ሰነበታችሁ የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን........የአባቶቻችን የጠበብት ኢትዮጵያውያን የእዉቀት እና የስነ አእምሮ ስፋት ና ጥልቀት ምን እንደሆነ የሚያሳየን፤ጥበብን እና እውቀትን የህይወታቸው አንዱ እና ዋነኛው ክፍል አድረገው ለዘመናት በሚያስደንቅ የጥበብ አውድ ውስጥ የኖሩት አባቶች የኢትዮጵያን ልዕልና ያሳዩን በምን ያህል ርቀት እንደሆነ የሚነግረን በተለየ ደግሞ የቤተክህነት ሰዎች ጥበብ እና እወቀት እግዚአብሄር አብዝቶ ያደላቸው ስለመሆናቸው ከሚያሳስበን አንዱና ዋነኛው ጉዳይ አንዱ የመገለጥ ግዜያቸውን እየጠበቁ ያሉት በኢትዮጵያ የተሰወሩት ዘጠኙ ፒራሚዶች ናቸው.... በዛሬው መርሀግብራችን ታዲያ እነዚህ የተሰወሩት ዘጠኙ የፒራሚድ ከተሞች ለምን ተሰሩ፣ እንዴት ተሰሩ፣ መቼ ተሰሩ የሚለውንና መቼስ ይገለጣሉ የሚሉትን ጥያቄዎች እና ሌሎችንም ነገር አክለው በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ምርምር ያደረጉትን የአባ ተስፋስላሴ ሞገስን መፅሀፍ በማጣቀስ ስለ ተሰወሩት ዘጠኙ የፒራሚድ ከተሞች እናወራለን፣
ስለምትመለከቱን አብዝቶ ደስ አለን ቪዲዮውን ሼር በማድረግ እናንተ ያገኛችሁትን እውቀት ለሌሎች አሳውቁ። በሀሳቡ ላይ አስተያየት ካሎት ይጻፉልን እናመሰግናለን፡፡ ይህ ግዜ ቲዩብ ነው ይህንን የግዜ ቲዩብ ዝግጅት ዘወትር እንዲደርሶ የመርሀ ግብራችን ቤተሰብ ይሁኑ በይነመረባችንን ይጎብኙት ሰላም ይኑረን ተስፋን አንጣ፡፡
Негізгі бет Ойын-сауық የተሰወሩ የፒራሚድ ከተሞች በኢትዮጵያ የት የት ይገኛሉ? ከግብፅ ፒራሚድ ጀርባ ኢትዮጵያዉያን
Пікірлер: 152